ጉዞዎን ያቅዱ

ወደሚፈልጉት ኣድራሻ ለመድረስ እንዲረዳዎ የጉዞ እቅድ ማዘጋጃ ቅፃችንን የጊዜ ሰሌዳችንንና የትራንስሊንክ ማቀላጠፊያ app ይጠቀሙ። የህዝብ ትራንስፖርት በሚጠቀሙበት ወቅት ከሚፈጥረው ጫና ማስወገድ የሚያስችሉ ቀላል መንገዶች ኣሉ።

ከስራ ሰዓት ውጭና ልዩ ዝግጅት በሚካሄድበት ቀንም በዓይነታቸው ልዩ የሆኑ ኣገልግሎቶች እንሰጣለን። ቀደም ብለው ማቀድ ያለብዎት መሆኑን ያስታውሱ፤ እነዚህ ልዩ ኣገልግሎቶች መቼ እንደሚከናወኑ፣ በምን ያህል ጊዜ እንደሚከናወኑና ከየት ጀምሮ መከታተል እንዳለብዎት ይወቁ።

ከኛ ጋር ይጓዙ

ወደ ደቡባዊ ምስራቅ ክዊንስላንድና ወደ ክዊስላንድ የገጠር ኣካባቢ በህዝብ ትራንስፖርት መጓዝ በጣም ቀላል ነው።

ለመጓዝ በሚወጡበት ቀን ከመውጣትዎ በፊት የTranslink website ሳያዩ ኣይውጡ ምክንያቱም ኣንዳንዴ ጉዞዎን ሊያሰናክሉ የሚችሉ የኣገልግሎት መቆራረጦች ሊኖሩ ይችላሉና።

ስለሚከተሉት ነገሮችም መረጃ ኣለን።.

ስለቲኬቶችና ዋጋቸው

ቲኬቶች

በክዊንስላንድ ደቡባዊ ምስራቅ go cardን ፣ seeQ card፣ Gold Coast go explore card ወይም የወረቀት ቲኬት በመጠቀም በTranslink መጓዝ ይችላሉ።

  • go cardን መጠቀም የወረቀት ቲኬት ከመጠቀም በ30% ይቀንሳል። ለመጠቀሙ በጣም ቀላልና ሂሳቡንም በትክክልና በቀላሉ ያሰላዋል። ይሄውም የሚተላለፈውን፣ ተሳፋሪ የሚቀንስበትንና እንዲሁም የብዙ ጊዜ ተጓዥ ቅናሽንም ሁሉ ኣስልቶ ሂሳቡን ከቀነሰ በኋላ ከወጪ ቀሪውን ካርድዎ ላይ ያስቀምጣል። በየጊዜው በኣጠገብዎ ባለው go card ጣቢያ ላይ ወይም በኣውቶማቲክ ላይ በላዩ እንዲሞላ ኣድርገው ያዘጋጁት። ስለዚህ በማናቸውም ሰዓት ለመጓጓዣ የሚሆን በቂ ገንዘብ ካርድዎ ውስጥ ይኖራል ማለት ነው።
  • የGold Coast go explore card በጎልድ ኮስት ለሚጓዙ ጎብኚዎች በጣም ጥሩ ነው። የኣንድ ሙሉ ቀን የትራምና የኣውቶቡስ ጉዞ ኣለምንም ገደብ ያስገኛል። ወደ ቴም ፓርክና ወደ ጎልድ ኮስት ኣየር ማረፊያ የሚኖረውን ጉዞ ብቻ ያካትታል።
  • የወረቀት ቲኬት ደጋግመው ለማይጓዙና ለኣንድ ጊዜ ጉዞ ብቻ ለሚጓዙ ወይም ለኣጭር ጊዜ ለሚመጡ ጎብኚዎች በኣውቶቡስ በባቡር በጀልባ ወይም በትራም መጓዝ ያስችላቸዋል። ኣንድ የወረቀት ቲኬት በኣውቶቡስ፣ በጀልባ፣ በባቡር ወይም በትራም ጣቢያዎች በሚሳፈሩበት ሰዓት መግዛት ይችላሉ።

go card በክዊንስላንድ የገጠር ኣካባቢዎች ካርዱን ማግኘት ኣይችሉም። የወረቀት ቲኬቶች በህዝብ ትራንስፖርት ኣገልግሎት ላይ ማግኘት ይችላሉ።

የቲኬት ዋጋ

የቲኬት ዋጋ የሚወሰነው እርስዎ በመጓዙባቸው ቀጠናዎች ልክ ነው።ዝርዝሩን current fares. በሚለው ላይ ይመልከቱ።

የቅናሽ የቲኬት ዋጋ ተጠቃሚዎች ከኣዋቂዎቹ የቲኬት ዋጋ በ50% የቀነሰ ሲሆን ይሄንን ካርድ የያዙ ኣንዳንድ ተጓዦች በTranslinkና በqconnect, እንዲሁም በገጠሩ የየጀልባ ኣገልግሎት በነፃ የመጓዝ እድል ያገኛሉ።

በደቡባዊ ምስራቅ ክዊንስላንድ የሚጓዙባቸውን የቀጠናዎች ብዛት ለማስላት ከሚጓዙበት ትልቁ ቀጠና ትንሹን ቀጠና በመቀነስ በላዩ ላይ ኣንድ መደመር ብቻ ነው።

የያንዳንዱን መስመር የጉዞ ሂሳብ ለማስላት የጉዞ ማቀጃችንን (journey planner) መጠቀም ይችላሉ።

ስለ Translink

የኣውቶቡስ የባቡር የጀልባና የትራም ኣገልግሎቶችን በማቅረብ እናቀናጃለን ። በተጨማሪም ለደንበኞች መረጃ በመስጠት የቲኬት ሽያጭ ማካሄድና የመጓጓዣ መሰረተ ልማቶችን የመምራት ሃላፊነት ኣለብን።

የTranslink የኣገልግሎት መረብ የደቡባዊ ምስራቅ ክዊንስላንድ ኣካባቢዎችን ( ማለትም ብሪዝበን ፣ ኢፕስዊች ፣ ሳንሻይን ኮስትና ጎልድ ኮስት ኣካባቢዎችን ያካትታል) በተጨማሪም በኣንዳንድ በተመረጡ የክዊንስላንድ የገጠር ኣካባቢዎችም ኣገልግሎት እንሰጣለን።

ደቡባዊ ምስራቅ ክዊንስላንድ

Translink በ8 የደቡብ ምስራቅ ክዊንስላንድ ቀጠናዎች ከሰሜን ጊምፒ እስከ ደቡብ ኮሉንጋታ እንዲሁም በደቡብና በምዕራብ እስከ ሄልደን ይሸፍናል።

የክዊንስላንድ የገጠር ኣካባቢዎች

የኣገልግሎት መረባችን በክዊንስላንድ ኣካባቢ ያለውን ኬይን ፣ ማኬይና ትዉምባና ታውንስቪል የመሳሰሉትን የገጠር ኣካባቢዎችን ያካትታል።

ያግኙን

የግብረ መልስ መጠየቂያ ቅፃችን ይጠቀሙ። ጥያቄ ካልዎት ወይንም እኛን ሊጠቁሙን የሚፈልጉት ቅሬታ ካለ፣ ጥያቄዎም ስለ go card, ከግለሰብ ምስጢር ኣጠባበቅ ምክንያት ስለሚያያዝ ደውለው ይንገሩን።

በኣውስትራሊያ ከየትኛውም ቦታ በ 13 12 30 ደውለው ያነጋግሩን ወይም ደግሞ ከኣውስትራሊያ ውጭ ከሆነ ያሉት ደግሞ በ +61 7 3851 8700 ደውለው ያነጋግሩ። በእንግሊዝኛ በደንብ ማነጋገር የማይችሉ ከሆነ ኣስተርጓሚ ያለበት የሶስትዮሽ እንዲፈቀድልዎት መጠየቅ ይችላሉ።.

ጥየቄዎን በ Facebook, በTwitter, ወይም በብሪዝቤን የጎብኝዎች ማእከልን (Visitor Information Centre) ያነጋግሩ

ጠቃሚ መረጃዎች